Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ልዩነቶች ላይ ከማማተር ይልቅ አንድነትን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ማተኮር ይገባል – አቶ ጥላሁን ከበደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አለመግባባትን ሊያሰፉ በሚችሉ ጥቃቅን ልዩነቶች ላይ ከማማተር ይልቅ አንድነትን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ማተኮር ይገባል አሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ይህንን ያሉት በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው ክልል አቀፍ የሰላም፣ የልማትና የአንድነት ህዝባዊ ጉባኤ ላይ ነው።

የመተባበርና የመተጋገዝ እሴቶቻችንን በማጎልበት ክልላችንን የብልጽግና ተምሳሌት እናደርጋለን ያሉት ርዕሰ  መስተዳደሩ÷ ክልሉ የተጋመደ ማንነትና የማይለያይ ሕዝብ ባለቤት በመሆኑ አንድነቱን በማጠናከር የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ማስቀጠል ይገባል ብለዋል፡፡

የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጫላ በበኩላቸው÷ የሕዝብ ተጠቃሚነትን በማስቀደም አዳጊ ፍላጎታቸው ምላሽ እንዲያገኝ የክልሉ መንግስት የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

መንግስት ዘርፈ ብዙ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በመስራት በርካታ ስኬቶች ማስመዝገብ መቻሉንም ጠቁመዋል።

በመለሰ ታደለ

Exit mobile version