Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ …

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አሰልጣኝ ገብረመድህን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ስማቸውን በደማቁ ማጻፍ ከቻሉ አሰልጣኞች መካከል ከቀዳሚዎቹ አንዱ ነው፡፡

የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዓመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ተብሎ መመረጡ አይዘነጋም፡፡

አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ኢትዮጵያ መድን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲያነሳ በማድረግ በኢትዮጵያ መድን ስፖርት ክለብ ታሪክ ውስጥ ስሙን በወርቅ ቀለም ጽፏል፡፡

ከምስረታው ጀምሮ በሀገሪቱ ታላላቅ አሰልጣኞች የተመራው ኢትዮጵያ መድን በመጨረሻም በአሰልጣኝ ገብረመድህን መሪነት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍ አድርጎ አንስቷል፡፡

አሰልጣኝ ገብረመድህን በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ታሪክ ከሶስት የተለያዩ ክለቦች ጋር የሊጉን ዋንጫ ማንሳት ችሏል፡፡

ታሪኩን ይበልጥ ለየት የሚያርገው ደግሞ ሶስቱም በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫውን ማንሳት የቻሉት በእርሱ የአሰልጣኝነት ዘመን መሆኑ ነው፡፡

ከጅማ አባ ጅፋር እና መቐለ 70 እንደርታ ጋር ከዚህ ቀደም ሻምፒዮን መሆን የቻለው አሰልጣኙ÷ አሁን ደግሞ ከኢትዮጵያ መድን ጋር ይህንን ታሪክ መስራት ችሏል፡፡

ይህም በሊጉ ታሪክ ከሶስት የተለያዩ ክለቦች ጋር የሊጉን ዋንጫ ያነሳ ብቸኛው አሰልጣኝ ያደርገዋል፡፡

የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአሁኑ የኢትዮጵያ መድን አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ሻምፒዮን ከሆነባቸው ክለቦች በተጨማሪ የተለያዩ የሊጉን ክለቦች ማሰልጠኑ ይታወሳል፡፡

በተጫዋችነት ዘመኑ ኢትዮጵያ የመካከለኛው እና ምስራቅ አፍሪካ ዋንጫን ዝምባብዌን አሸንፋ ዋንጫውን ከፍ አድርጋ ስታነሳ ገብረመድህን የፊት መስመሩን ከመምራት ባለፈ የብሔራዊ ቡድኑ አምበልም ነበር፡፡

ገብረመድህን ኃይሌ በተጫዋችነት ዘመኑ በሚያደርገው ድንቅ እንቅስቃሴ በበርካቶች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆት ተችሮታል፡፡

አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ በአሰልጣኝነት ሕይወቱም በተለያዩ ክለቦች ሻምፒዮን በመሆን የራሱን ደማቅ ታሪክ እየጻፈ ይገኛል፡፡

በወንድማገኝ ፀጋዬ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version