አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የክረምት ወራት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እና የወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ተካሄደ፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ፣ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እንዲሁም ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎች፣ ወጣቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
‘በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ’ በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ አቶ አወል አርባ እንዳሉት፤ በጎነት ክፍያ የማይጠይቅ ምንዳው ከፍ ያለ ነው።
አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርን በመተግበር ረገድ ወጣቶች ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው ገልጸው፤ በወሰን ተሻጋሪ ወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
ወጣቶች ወደ ሌላ ክልል በመሔድ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማከናወናቸው ህብረብሔራዊነትን እንደሚያጠናክር ገልጸው፤ አንዱ የሌላውን አካባቢ የሚያውቅበት ዕድል ይፈጥራል ነው ያሉት።
የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ከግለሰብ ጀምሮ እስከ ሀገር ድረስ የጎላ አስተዋጽኦ የሚያበረክት እንደሆነ ተናግረዋል።
ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ በመሳተፍ የዜግነት ግዴታቸውን በመወጣት ለሀገር እና ለወገን አስተዋጽኦ ማበርከት አለባቸው ብለዋል።
በመርሐ ግብሩ ወጣቶች በክልሎች በመንቀሳቀስ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚያከናውኑ ሲሆን፤ ደም ልገሳ፣ አረንጓዴ አሻራን ማኖር፣ የአረጋውያንን እና የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስን ጨምሮ የተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ይከናወናሉ።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!