አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ባካሄደው ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
በዚሁም የሲዳማ ቡና ስፖርት ከለብ የታገዱ ተጫዋቾችን በማሰለፍ ያሸነፈው የኢትዮጵያ ዋንጫ በፎርፌ ተሸናፊ ሆኖ ዋንጫው ለወላይታ ድቻ ተመላሽ እንዲደረግ እና የወላይታ ድቻ ስፖርት ክለብ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የ2025/26 የውድድር ዘመን ተሳታፊ እንዲሆን ውሳኔ አሳልፏል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የፋይናንስ አስተዳደር መመርያን በመተላለፍ የተወሰነባቸውን ውሳኔ መቻል ስፖርት ክለብ፣ ሀዋሳ ከተማ ስፖርት ክለብ እና ሲዳማ ቡና ስፖርት ክለቦች ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መተዳደርያ ደንብ ውጪ ጉዳዩን ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት በመውሰድ ክስ በመመስረት እና ውሳኔውን በማሳገድ እግድ የተጣለባቸው ተጫዋቾች በሦስቱ ክለቦች ተሰልፈው እንዲጫወቱ መደረጉን በመገምገም ውሳኔ ሰጥቷል።
በዚህም ሦስቱም ክለቦች የፍትህ አካላትን ውሳኔ በአስቸኳይ ተግባራዊ እንዲያደርጉ እና መሰለፍ የሌለባቸውን የታገዱ ተጫዋቾች ተጠቅመው ያጫወቷቸው ጨዋታዎችን በሙሉ በፎርፌ ተሸናፊ እንዲሆኑ እና የተጣለባቸውን የገንዘብ ቅጣት በመክፈል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወስኗል።
ሌሎቹ 14 ክለቦች የፋይናንስ መመሪያውን ተከትለው ስለመስራታቸው ምርመራ እንዲደረግ እና ምርመራው እስከሚጠናቀቅ በፕሪሚየር ሊግ ክለቦች መካከል የሚከናወን የተጫዋቾች የዝውውር እንቅስቃሴ ታግዶ እንድቆይ ተወስኗል።
በ2018 የሊግ ውድድር በ2017 የፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊ የነበሩ 18 ክለቦች እና ከከፍተኛ ሊግ ያደጉ ሁለት ቡድኖችን በማካተት በ20 ክለቦች መካከል እንዲካሄድ እና በውድድር ዓመቱ አራት ክለቦች ወደ ከፍተኛ ሊግ እንዲወርዱም ነው የተወሰነው።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!