አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 5 ፣2012ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የክረምት ወራትን መግባት ተከትሎ ወደ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር የገቡ ደለልና ደረቅ ቆሻሻዎችን የማፅዳት ስራ እየተከናወነ መሆኑ ተገለፀ።
የከተማዋ መንገዶች ባለስልጣን በከተማዋ መንገዶች ላይ የሚከሰት የጎርፍ መጥለቅለቅ ዋነኛ መንስኤ የሆነው የዝናብ ውሃ መውረጃ መስመሮች በቀላሉ በማይበሰብሱ ደረቅ ቆሻሻዎችና የፕላስቲክ ውጤቶች የተደፈኑ መሆናቸውም ነው የገለጸው፡፡
በመሆኑም ይህንን እና ተያያዥ ችግሮችን ለመፍታት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓትና በሌሎች ምክንያቶች ጉዳት የደረሰባቸውን የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮችን የመጠገንና የማፅዳት ስራ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ ነው መሆኑን አመላክቷል፡፡
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

