Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጋምቤላ ክልል 5 ሺህ ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ላከ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2017 በጀት ዓመት እስካሁን 5 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አቅርቤያለሁ አለ የጋምቤላ ክልል ማዕድን ኤጀንሲ።
የኤጀንሲው ም/ሃላፊ ኤሊያስ ገዳሙ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት ÷ በክልሉ ያለውን እምቅ የማዕድን ሃብት በሚገባ ጥቅም ላይ ለማዋል በትኩረት እየተሰራ ነው።
በተለይም የወርቅ ምርትን ለማሳደግ በትብብር መሰራቱን ጠቅሰው፥ እስካሁንም 5 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ መቅረቡን ተናግረዋል።
አፈጻጸሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ8 እጥፍ ብልጫ እንዳለው አስረድተዋል።
ለዚህም ሀገር በቀል የማክሮ የኢኮኖሚ ማሻሻያው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ነው የተናገሩት።
የኢኮኖሚ ማሻሻያው ሕገ ወጥ የወርቅ ማዕድን አዘዋዋሪዎችን በመቀነስ ወደ ብሔራዊ ባንክ የሚገባውን ወርቅ መጠን ማሳደጉን አስገንዝበዋል።
በክልሉ አሁን ላይ ያለው አስተማማኝ ሰላም የማዕድን ዘርፉ እንቅስቃሴ እንዲጨምር አድርጓልም ነው ያሉት።
በመላኩ ገድፍ
Exit mobile version