Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በክልሉ በመኸር እርሻ 849 ሺህ 833 ሔክታር መሬት ይለማል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በመኸር እርሻ 849 ሺህ 833 ሔክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ እየተሰራ ነው።

የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የእርሻ ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አድማሱ አወቀ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በምርት ዘመኑ ከመኸር አዝመራ ከ68 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ታቅዷል።

በዚህም በአዝዕርት ሰብሎች 647 ሺህ 810 ሄክታር መሬት ለማልማትና 15 ሚሊየን 176 ሺህ 418 ኩንታል ምርት ለማግነት መታቀዱን ጠቁመዋል።

በተመሳሳይ በአትክልትና ስራስር ሰብሎች 90 ሺህ 904 ሄክታር በማልማት 20 ሚሊየን 693 ሺህ 877 ኩንታል ምርት ለማግነት እንዲሁም በፍራፍሬ ሰብሎች 80 ሺህ 417 ሄክታር መሬት በማልማት 22 ሚሊየን 622 ሺህ 252 ኩንታል ምርት ለማግኘት ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

በተጨማሪም በመኸር ወቅት በሆርቲካልቸርና በአዝዕርት ሰብሎች ኩታ ገጠም እርሻ በመተግበር ምርታማነቱን ከነበረበት 36 ነጥብ 9 ኩንታል በሄክታር ወደ 58 ነጥብ 4 ኩንታል በሄክታር በማሳደግ 186 ሺህ 803 ሄክታር ለማልማትና 10 ሚሊየን 918 ሺህ 654 ኩንታል ምርት ለማግኘት መታቀዱን ነው ያስረዱት።

ዕቅዱን ለማሳካት የቴክኖሎጂና ግብዓት አቅርቦት፣ የክላስተር እርሻዎች ልየታና ዝግጅት፣ የማሳ ልየታና የባለሙያዎች ድጋፍ የመስጠት እንዲሁም አልሚውን ለይቶ ለመንቀሳቀስ የዝግጅት ሥራዎች በስኬት መከናወናቸውን አብራርተዋል።

በመኸር እርሻ በክልሉ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገር የገቢ ምርቶችን በራስ አቅም ማምረትና የኢንዱስትሪ ግብዓት የሚሆኑ ምርቶችን ለማሳደግ እንደሚሰራም ጠቁመዋል።

አርሶ አደሩም የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግና ከባለሙያዎች የሚሰጠውን ድጋፍ በመተግበር ለውጤታማነቱ እንዲተጋ ጥሪ አቅርበዋል።

በአድማሱ አራጋው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version