Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በክልሉ ከዘንድሮው የበልግ እርሻ ከ13 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከዘንድሮው የበልግ እርሻ ከ13 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል።

ከተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የተውጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች በክልሉ የተሰሩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ይገኛል።

የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ አለሙ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ በበልግ እርሻ ከ394 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር ተሸፍኗል።

ከዚህም ውስጥ ከ269 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በበቆሎ፣ ከ28 ሺህ ሄክታር በላይ በሩዝ ሰብል የተሸፈነ እንዲሁም ቀሪው በሌሎች ሰብሎች የተሸፈነ መሆኑን አብራርተዋል።

በዘር ከተሸፈነው መሬት ውስጥ 77 ሺህ ሄክታር ማሳ በኩታ ገጠም የታረሰ እንደሆነም ጠቁመዋል።

በዘንድሮው የበልግ እርሻ በክላስተር የተደራጁ ከ86 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች መሳተፋቸውን ገልጸው÷ የአርሶ አደሩ በኩታ ገጠም የማረስ ልምድ እየጨመረ መጥቷል ብለዋል።

በተስፋዬ ምሬሳ

Exit mobile version