Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ ለ174 መገናኛ ብዙሃን ፈቃድ ተሰጥቷል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከሀገራዊ ሪፎርሙ ወዲህ ለ174 መገናኛ ብዙሃን ፈቃድ ተሰጥቷል አለ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን።

ባለስልጣኑ የተቋማዊ ሪፎርም ስራዎችን አፈጻጸም ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላትና የዴሞክራዊ ተቋማት የጋራ መድረክ ላይ ሪፖርት አቅርቧል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዮናታን ተስፋዬ እንዳሉት÷ ባለስልጣኑ ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅና የሚዲያ ነፃነትን የሚያረጋግጡ ሥራዎችን ሰርቷል።

የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃን ለመከላከል በአዋጅ የተሰጠውን ስልጣንና ኃላፊነት ለመወጣት በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን አብራርተዋል።

ባለስልጣኑ የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ መወጣት የሚያስችል የሕግ ማሻሻያ ማድረጉንም ነው ያስረዱት፡፡

ከለውጡ በፊት በዘርፉ የሚሰሩ የሙያና ሲቪክ ማህበራት ከ6 የማይበልጡ እንደነበሩ ጠቅሰው÷ ለውጡን ተከትሎ 38 ማህበራትና አደረጃጀቶች ወደ ሥራ መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡

ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ በትምህርት በማህበረሰብ ሬዲዮ፣ በሃይማኖት፣ በቴሌቪዥንና በሬዲዮ እንዲሁም በዲጂታል ሚዲያ ላይ ፈቃድ ወስደው የሚሰሩ መገናኛ ብዙሃን ቁጥር መጨመሩን ጠቁመዋል፡

በዚህም ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ 174 አዳዲስ መገናኛ ብዙሃን ከባለስልጣኑ ፈቃድ ወስደው ወደ ስራ እንደገቡ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የመገናኛ ብዙሃኑ የቋንቋ ተደራሽነትም ከነበረበት 39 አሁን ላይ ወደ 63 ከፍ ማለቱን ም/ዋና ሥራ አስፈፃሚው አመልክተዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version