አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሐረር ከተማ ከፍሳሽ ጋር በተገናኘ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት አንድ ቢሊየን ብር ተመድቦ ወደ ሥራ ተገብቷል አሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ።
የክልሉ መስተዳድር ም/ቤት በሐረር ከተማ ተግባራዊ በሚደረገው የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ጣቢያ እና የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ፕሮጀክት ላይ መክሯል።
አቶ ኦርዲን በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በ1 ቢሊየን ብር ወጪ ተግባራዊ የሚደረገው የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ጣቢያ እንዲሁም የጁገል ዙሪያ የቆሻሻና የውሃ ማጣሪያ መስመር ፕሮጀክቶች ከተማውን ለማዘመን ከፍተኛ አበርክቶ አላቸው።
በተለይ ፕሮጀክቱ የኮሪደር ልማቱን የተሟላ እንደሚያደርግ እና የከተሜነት ሕይወትን ይበልጥ ማዘመን እንደሚያስችል ነው ያስረዱት፡፡
ፕሮጀክቱ ከፍሳሽ ጋር በተገናኘ የሚስተዋሉ ችግሮችን እንደሚፈታ ጠቁመዋል÷ በአጭር ጊዜ ለማስጀመር በቅንጅትና በትብብር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በፍጥነት ለመጀመር ከግንባታው ጎን ለጎን አስፈላጊ መሰረተ ልማቶችን የማሟላት ሥራ እንዲከናወን አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
በተስፋዬ ኃይሉ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

