አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ያሏትን ሀብቶች ለማስተዋቅውና ለመሸጥ የሚያስችል ’ቪዚት ኢትዮጵያ’ የተሰኘ ሀገር በቀል የግብይት መተግበሪያ ቱሪዝም ይፋ ተደርጓል፡፡
የቱሪዝም ሚኒስትር ስላማዊት ካሳ በማብሰሪያ መርሐ ግብሩ ላይ እንዳሉት፥ መተግበሪያው በሃገራችን የሚገኙ መዳረሻዎችንና የቱሪዝም አገልግሎትን በስፋት ለማስተዋወቅ ያግዛል፡፡
ሚኒስቴሩ በሀገራችን የሚገኙ ተፈጥሯዊና ባህላዊ ቅርሶችን በማልማትና በማስተዋወቅ የተለያዩ ተግባራትን እየከወነ መሆኑን ጠቅሰው፥ መተግበሪያውን በማዘጋጀት ኢንሳ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ በበኩላቸው፥ የዲጂታል ዘመን የሚጠይቀውን ማሟላትና ተወዳዳሪ መሆን የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ ነን ብለዋል፡፡
ቪዚት ኢትዮጵያ የተሰኘው አዲሱ መግበሪያ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው መዳረሻዎችን ደግሞ በአንድ ጊዜ ለማስተዋወቅ ትልቅ ሚና እንዳለውም ነው ዳይሬክተሯ የገለጹት፡፡
መተግበሪያው የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ አስጎብኚ ድርጅቶች፣ ሆቴሎችና በቱሪዝም ዘርፍ ያሉ ተዋናዮችን በአንድ በይነ መረብ እንዲተሳሰሩ ማድረግ ያስችላል።
በሃይማኖት ወንድይራድ

