Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመዲናዋ 233 ቢሊየን ብር ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት 233 ቢሊየን ብር ገቢ ሰበሰበ፡፡

የአስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንዳሉት፤ በበጀት ዓመቱ 241 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ የዕቅዱን 96 ነጥብ 5 በመቶ ማሳካት ተችሏል።

በዚህም 233 ቢሊየን ብር ገቢ በመሰብሰብ ከባለፈው በጀት ዓመት የ83 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ብልጫ ተሰብስቧል።

ካለፈው ዓመት አንጻር 57 በመቶ እድገት በከተማዋ ገቢ ላይ እድገት ያሳየ ነው ብለዋል።

ከዕቅዱ አንጻር ያልተሰበሰበው 8 ቢሊየን ብር ከእርዳታ እና ብድር ይገኛል ተብሎ በተጨማሪ በጀት የታወጀ እንደነበር አስታውሰዋል።

ለውጥና እድገት በራስ አቅም ሲሆን መሰረቱ ሰፊ፤ ምሰሶውም ጠንካራ ይሆናል ያሉት ከንቲባዋ፤ ለነዋሪዎች፣ ግብር ከፋዮች፣ የገቢዎች ቢሮ ሰራተኞችና አመራሮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

ነገም አቅማችን እናተዉ ናችሁና ፤ ችግሮችን እያረምን በራስ አቅም፣ በትብብር፣ በጠንካራ እምነት እና የስራ ባህል የመራናት ከተማችን እድገት ይቀጥላል ሲሉም አረጋግጠዋል።

Exit mobile version