Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሐረሪ ክልል 300 የአቅመ ደካማ ወገኖች ቤት ይታደሳል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሐረሪ ክልል የዘንድሮ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 300 የአቅመ ደካማ ወገኖች ቤት ይታደሳል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የክረምቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት በማደስ ሥራ በይፋ ተጀምሯል።

አቶ ኦርዲን በድሪ በወቅቱ እንዳሉት÷ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካማ ወገኖችን ችግር በመቅረፍ ረገድ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል።

እርስ በርስ በመደጋገፍ የኢኮኖሚ አቅማቸው ውስን የሆኑ ዜጎችን ችግር መጋራት ከሁሉም ይጠበቃል ሲሉ ገልጸው÷ ዘንድሮ በክልሉ በገጠር እና በከተማ 300 የአቅመ ደካማ ወገኖች ቤት ይታደሳል ብለዋል።

በዘንድሮ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በተለያዩ መርሐ ግብሮች 150 ሺህ ዜጎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑም አመላክተዋል፡፡

በተስፋዬ ኃይሉ

Exit mobile version