Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በቢሾፍቱ እያስመረቀ ነው።

ዩኒቨርሲቲው በ2017 ዓ.ም በምህንድስና፣ በጤና ሳይንስ እና በማህበረሰብ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ (ኢ/ር)፣ የሠራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ የመንግስት አመራሮች እንዲሁም የወዳጅ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎችና የባለድርሻ አካላት ተወካዮች ተገኝተዋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ብ/ጄ ከበደ ረጋሳ÷ ተመራቂዎች በትምህርት ቆይታቸው ያካበቱትን እውቀት ተጠቅመው በሚሠማሩበት ሙያ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

ዩኒቨርሲቲው ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው የጥናትና ምርምር ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ጠቅሰው÷ ተቋማቸው የሠራዊቱን የግዳጅ አፈፃፀም ወደላቀ ደረጃ ለማሳደግ እየሠራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በየሻምበል ምህረት

Exit mobile version