አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲዳማ ክልል በቀጣይ ሁለት ወራት በሚከናወነው የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት መርሐ ግብር ከ800 ሺህ በላይ በጎ ፍቃደኞች ይሳተፋሉ፡፡
መርሐ ግብሩ የማጠናከሪያ ትምህርት፣ የቤት እድሳት፣ የደም ልገሳና ችግኝ ተከላን ጨምሮ በ14 ዘርፎች ላይ ትኩረት በማድረግ ይከናወናል።
በዚህም የ3 ሺህ ቤቶች የእድሳትና አዲስ ግንባታ ስራን ጨምሮ 5 ሺህ ዩኒት ደም በበጎ ፍቃድ ለመሰብሰብ ታቅዷል።
በዘመቻ ስራው ከ1 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑና ከ1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ተግባር እንደሚከናወን የክልሉ ሴቶች፣ ወጣቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ለፋና ዲጂታል ገልጿል።