አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲኮ መንዶ ገዳ ሕግ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት በምዕራብ አርሲ ዞን ነጌሌ አርሲ ወረዳ እየተካሄደ ነው፡፡
በጉባዔው የአርሲ ገዳ በቀጣይ መካሄድ ያለበትን ሁኔታ እና በአርሲ ውስጥ የጋብቻ ሕጎች ምን መሆን እንዳለባቸው የሚደነግጉ ሕጎች ይወጣሉ፡፡
በተጨማሪም ጉባዔው ጉማ የሚጨርስበት ሕግ፣ ሰላም የማስፈን ሕግ እና ትውልዱን ወደ ባሕሉና እሴቱ መመለስ የሚያስችሉ ሕጎች ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
በስምንት ዓመት አንድ ጊዜ የሚካሄደው የሲኮ መንዶ ጉባዔ ለሁለት ቀናት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክር ተመላክቷል፡፡
በጉባዔው የተለያዩ ሕጎች የሚሻሻሉ ሲሆን÷ በማሕበረሰቡ ባሕልና እሴት ላይ በጥልቀት ውይይት እንደሚደረግም ተጠቁሟል፡፡
የገዳ ሥርዓት በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባሕል ተቋም (ዩኔስኮ) በማይዳሰስ ቅርስነት መመዝገቡ ይታወሳል፡፡
በፌናን ንጉሴ