Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ወደ ናይጄሪያ አቀና

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ የአፍሪካ ከ20 እና 18 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ለመሳተፍ ወደ ናይጄሪያ አቡኩታ አቅንቷል።

በፈረንጆቹ ከሐምሌ 16 እስከ 20 ቀን 2025 በናይጄሪያ አቡኩታ ለሚካሄደው የአፍሪካ ከ20 እና 18 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፈው የአትሌቲክስ ልዑክ ወደ ናይጄሪያ አቡኩታ አምርቷል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሸኝኝት ተደርጎለታል።

ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ዛሬ እኩለ ሌሊትም ሁለተኛ ዙር የወጣቶች አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን ወደ ናይጄሪያ እንደሚጓዝ ታውቋል።

Exit mobile version