Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ በዲጂታል ዘርፍ ጥሩ አፈፃፀም ካላቸው ሀገራት መካከል ነች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 25ኛው የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የፋይናንስ ሚኒስትሮች ስብሰባ በኬኒያ ናይሮቢ በትናንትናው ዕለት ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ የተሳተፉ ሚኒስትሮች ዲጂታል ትስስርን ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

በፈረንጆቹ 2023 ስለፀደቀው የዲጂታል ውህደት እና የፖሊሲ ማዕቀፍ ሚኒስትሮች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚህም ሀገራት ጥሩ አፈጻጸም በማስመዝገብ ላይ መሆናቸው የተመላከተ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ጥሩ አፈፃፀም ካላቸው ሀገራት መካከል አንዷ ነች ተብሏል፡፡

በምክክሩ የተሳተፉት የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በዲጂታል ውህደት እያስመዘገበች ያለችውን ዕድገት ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ በዲጂታል ዘርፍ የቴሌኮም ዘርፎችን ነፃ ማድረግ፣ የግል መረጃ ጥበቃ እና የሳይበር ደህንነት ህጎችን በማውጣት በርካታ ተግባራት ማከናወኗን ጠቁመዋል።

ከ19 ሚሊየን በላይ ዜጎች በዲጂታል መታወቂያ ስርዓት በመመዝገብ ውጤት ማምጣት መቻሉን ማብራራታቸውን ሚኒስቴሩ ለፋና ዲጂታል በላከው መረጃ አመላክቷል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version