Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከ600 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እየተገነባ የሚገኘው የሱስ ማገገሚያ ማዕከል…

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል የሱስ ማገገሚያ ማዕከል ግንባታ ከ600 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በፍጥነት እየተከናወነ ይገኛል።

ማዕከሉ በሚቀጥለው ዓመት ወደ አገልግሎት እንደሚገባ የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ሲሳይ ተበጀ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል፡፡

በአማራ ክልል ጤና ቢሮ የገንዘብ ድጋፍ እየተከናወነ የሚገኘው ማዕከሉ፥ አሁን ላይ የግንባታ ደረጃው 57 በመቶ መድረሱን ገልጸዋል፡፡

ሆስፒታሉ አገልግሎቱን እየሰጠ መሆኑን ጠቅሰው፥ በዚህም በርካታ ወጣቶች ከሱስ መውጣት እንደቻሉ አንስተዋል።

የቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል የሱስ ማገገሚያ ማዕከል ወደ አልግሎት ሲገባ ከሱስ ጋር ተያይዞ ችግር ውስጥ ላሉ ዜጎች መፍትሄ ይሰጣል ነው ተብሏል።

Exit mobile version