አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሐረሪ ክልል በሕገ ወጥ ነዳጅ ግብይት የተሳተፉ የነዳጅ ማደያዎች ላይ ርምጃ ተወሰደ፡፡
የክልሉ ንግድ ልማት አጄንሲ ሃላፊ ሸሪፍ ሙሜ እንዳሉት÷ በክልሉ ሕገ ወጥ የነዳጅ ግብይትን ለመቆጣጠርና ለመከላከል በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡
በተለይም የነዳጅ ዋጋ እንዲንርና እጥረት እንዲፈጠር እያደረጉ በሚገኙ ማደያዎች ላይ ክትትል በማድረግ ርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
ኤጀንሲው ባከናወነው የቁጥጥር ሥራም ሕገ ወጥ የነዳጅ ግብይት በፈጸሙ አራት ማደያዎች ላይ ርምጃ መወሰዱን ነው ያብራሩት፡፡
ርምጃው በነዳጅ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ በማድረግ እና የግብይት ሥርዓት መመሪያውን በመተላለፍ ሲገበያዩ በተገኙ ማደያዎች ላይ መወሰዱን አመልክተዋል፡፡
በዚህ መሰረትም ማደያዎቹ ከሁለት ወር እገዳ እስከ ገንዘብ መቀጣታቸውን ጠቁመው÷ በሕገ ወጥ ግብይት የሚሳተፉ ማደያዎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በተስፋዬ ሃይሉ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!