Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ስኬት ባንክ ካፒታሉን 9 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር አደረሰ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ስኬት ባንክ የ2024/25 በጀት ዓመት አጠቃላይ የካፒታል መጠኑን 9 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር አድርሷል።

ባንኩ የ2024/25 በጀት ዓመት አፈፃጸም እና የ2025/26 ዕቅድ ላይ የሚመክር ጉባኤ አካሂዷል፡፡

በ2024/25 በጀት ዓመት አጠቃላይ ካፒታሉን 9 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ያደረሰው ባንኩ፤ 19 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር አጠቃላይ ሀብት አስመዝግቧል፡፡

7 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰቡን ገልጾ፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 2 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ገቢ በማስመዝገብ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ትርፍ ማግኘቱን አስታውቋል።

የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዳምጠው አለማየሁ እንዳሉት፤ ባንኩ በአብዛኛዎቹ የሥራ አፈፃፀም መለኪያዎችም የላቀ አፈፃፀም አስመዝግቧል።

ከተለያዩ የሀገር ውስጥ እና በውጪ ሀገር ከሚገኙ ተቋማት ጋር በቀጣይነት አብሮ ለመስራት የሚያስችል ስትራቴጂካዊ ስምምነቶች እየተደረጉ እንደሆነም ጠቁመዋል።

የማህበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት አንፃር በበጀት ዓመቱ ከ56 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን ባንኩ ለፋና ዲጂታል በላከው መግለጫ አመላክቷል።

Exit mobile version