አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የምግብ ስርዓት ማሻሻያ ተግባራዊ መደረጉ ከምርታማነት እስከ ተጠቃሚው ድረስ አመርቂ ውጤት ተመዝግቧል አለ የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ማንደፎሮ ንጉሴ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ የምግብ ፍኖተ ካርታ በማዘጋጀት ከምርታማነት እስከ ተጠቃሚነት የዘለቁ ስራዎችን በመስራት የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እየሰራች ትገኛለች።
የምግብ ስርዓት ሽግግር ትግበራው ግብ እያንዳንዱ ዜጋ ጤናማ አመጋገብ በ2030 እንዲኖረው ማድረግ መሆኑን ጠቅሰው፤ ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ የሚያስችል ስራ እየተሰራ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር መሳይ ሀይሉ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ እንደ ሌማት ትሩፋት አይነት ትግበራዎች የምግብ ስርዓቱን በማሻሻል ረገድ ውጤት እንደታየባቸው አብራርተዋል።
ይህም ጤናማ አመጋገብን የመፍጠር ሂደት ላይ በጎ ጅምር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በክብረወሰን ኑሩ