Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በጉባኤውም የ2017 በጀት ዓመት የአስፈጻሚ አካላት፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት አፈፃፀም ሪፖርት እና ተያያዥ አጀንዳዎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግ ተመላክቷል።

እንዲሁም የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ለፋና ዲጂታል ገልጿል።

Exit mobile version