Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሚሊኒየም አዳራሽ በዘመናዊ መንገድ ሊገነባ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ ፓርክ ዴቨሎፕመንት ወይም በተለምዶ አጠራሩ ሚሊኒየም አዳራሽ ከአካባቢው የልማት ስራዎች ጋር በተጣጣመ መልኩ በዘመናዊ መንገድ ሊገነባ ነው።

የሚድሮክ ግሩፕ ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን እና ፕሮሞሽን ዳይሬክተር ሁናቸው ታዬ በሰጡ መግለጫ፤ አዲስ ፓርክ ዴቨሎፕመንት ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም የእሳት አደጋ አጋጥሞት እንደነበረ አስታውሰዋል።

ከሚሊኒየም መባቻ ጀምሮ በርካታ ሁነቶችን በማስተናገድ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው አዳራሹ ያለበትን አካባቢ ሊመጥን በሚችል ደረጃ በአዲስ መልክ ሊገነባ እንደሆነ ጠቁመዋል።

በዚህም ከታህሳስ ወር 2018 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ግንባታ የሚገባ መሆኑን አመልክተዋል።

ሚሊኒየም አዳራሽ በቅርቡ አጋጥሞት ከነበረው ችግር ወጥቶ ወደ መደበኛ አገልግሎቱ መመለሱን ጠቅሰው፤ አዲሱ ግንባታ እስኪጀመር ድረስ የተለመደውን አገልግሎት እየሠጠ ይቀጥላል ብለዋል።

በመሳፍንት ብርሌ

Exit mobile version