Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኬንያ አንድ ከፍተኛ የጤና ባለሥልጣን በኮቪድ-19 ሕይወታቸው አለፈ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኬንያ እየጨመረ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ አንድ ከፍተኛ የጤና ባለሥልጣን በኮቪድ 19 ህይወታቸው አልፏል ።

ካማኡ ሙጌንዳ የተባሉት እኝህ ባለስልጣን÷ በኬንያ የህክምና ምርምር ኢንስቲትዩት ምክትል ሃላፊ ከመሆናቸውም ባለፈ የሀገሪቱን የኮቪድ -19 ወረርሽኝ የምርመራ እና የክትባት ሙከራ መርሃ-ግብር በበላይነት ይመሩ ነበርም ተብሏል።

ሃላፊው በሀገሪቱ በጤና ሚኒስቴር ውስጥ ከሚሰሩና በወረርሽኙ ከተያዙ 450 በላይ ባለሙያዎች መካከል አንዱ መሆናቸው ተመላክቷል ፡፡

በሀገሪቱ በኮቪድ 19 ህይወታቸው ያለፈ የጤና ባለሙያዎች ቁጥር እኝህን ባለስልጣን ጨምሮ አራት መድረሱ ተነግሯል።

ኬንያ ምንም እንኳን የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር ጥብቅ እርምጃዎች ብትወስድም ባለፉት ሳምንታት የስርጭቱ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተገልጿል።

በኬንያ እስካሁን ከ28 ሺህ በላይ ሰዎች በበሽታው የተያዙ ሲሆን÷ ከ450 በላይ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ህይወታቸውን አጥተዋል ፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version