Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በክልሉ ከ14 ቢሊየን ብር በላይ ሃብት ያስመዘገቡ አልሚዎች ወደ ስራ ገብተዋል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በ2017 በጀት ዓመት ከ14 ቢሊየን ብር በላይ ሃብት ያስመዘገቡ አልሚዎች ወደ ስራ ገብተዋል አለ የክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ፡፡

‎የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ከበደ ተስፋዬ በክልሉ የኢንቨስትመንት ፍላጎት እየጨመረ መምጣቱን አስረድተዋል።

በ2017 በጀት አመት ወደ ኢንቨስትመንት የገቡ 114 ባለሀብቶች 14 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ሀብት ማስመዝገባቸውን ተናግረዋል፡፡

‎በቀጣዩ 2018 በጀት አመት በግብርና፣በአገልግሎት እና በኢንዱስትሪ ዘርፎች ከ180 በላይ ባለሀብቶችን ለማሰማራት ዝግጅት ተደርጓልም ነው ያሉት፡፡‎

‎በኢንዱስትሪ ዘርፍ መሰማራት የሚፈልጉ አልሚዎች ይበልጥ እንደሚበረታቱ ጠቁመው፥ ባለሀብቶች በክልሉ ያለውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም እንዲያለሙ ጥሪ አስተላልፈዋል ።

በ‎ቅድስት በርታ

Exit mobile version