አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሐረሪ ክልል በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ67 ሺህ በላይ ዜጎች ይሳተፋሉ አለ የክልሉ ሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ቢሮ ፡፡
የቢሮው ሃላፊ ረምዚያ አብዱልወሃብ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት ÷ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱን በ14 ዘርፎች ለሕብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው።
አረንጓዴ አሻራ፣ ጤና አገልግሎ፣ ቤት ግንባታና እድሳትን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ከ267 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱን ተናግረዋል፡፡
አሁን ላይም የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት፣ ደም ልገሳ እና ሌሎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ተግባራዊ እየተደረጉ ነው ብለዋል፡፡
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አብሮነትንና መተሳሰብን እንደሚያጠናክር ጠቁመው ÷ የማሕበረሰቡ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተሳትፎ እያደገ መምጣቱን አመልክተዋል፡፡
በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የክልሉ ሕዝብ በንቃት እንዲሳተፍም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በሶስና አለማየሁ