Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሕዳሴ ግድቡ ወደ ኢንዱስትሪ የሚደረገውን ጉዞ ያሳልጣል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ኃይል እያደገ ላለው የኢንዱስትሪ ዘርፍ የኃይል ፍላጎት ምላሽ በመስጠት ኢትዮጵያ ወደ ኢንዱስትሪ የምታደርገውን ጉዞ ያሳልጣል አሉ ምሁራን፡፡

ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ቆይታ የነበራቸው ምሁራን፤ ከግድቡ የሚመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይል የኢትዮጵያን የኃይል አቅርቦት በከፍተኛ ሁኔታ በማሳደግ ለአምራች ኢንዱስትሪ ጠቀሜታ እንደሚኖረው አብራርተዋል፡፡

በአዳማ ዩኒቨርሲቲ የኬሚካል ምህንድስና ትምህርት ክፍል መምህር መላኩ ተስፋዬ (ዶ/ር)፤ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ለአምራች ኢንዱስትሪው አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር ያስችላል ነው ያሉት፡፡

ኢንዱስትሪዎች ከዚህ ቀደም ከኃይል አቅርቦት ጋር ያጋጥማቸው የነበረውን ችግር በመፍታት የማምረት አቅማቸውን እንደሚያሳድጉም ጠቁመዋል።

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የመካኒካል ምህንድስና ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ጌታሁን ሶርሳ በበኩላቸው፤ የኃይል አቅርቦት ማደግ በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን ምርትን በብዛት እና በጥራት ለማምረት ያስችላል ብለዋል።

ህዳሴ ግድቡ ለኢንዱስትሪዎች የሚያስፈልገውን ኃይል በከፍተኛ ሁኔታ ስለሚሰጥ ኢትዮጵያ በዋጋም በጥራትም ከፍተኛ ተወዳዳሪ የሆኑ ምርቶችን ማምረት እንድትችል ያግዛታል ነው ያሉት።

እያደገ ላለው የኢንዱስትሪ ዘርፍ የኃይል ፍላጎት ምላሽ በመስጠት ሀገሪቱ ወደ ኢንዱስትሪ የምታደርገውን ጉዞ ያሳልጣል ሲሉም አስረድተዋል።

ኢትዮጵያ ከታችኛው የኢኮኖሚ ደረጃ ወደ መካከለኛው ገቢ ለመድረስ የምታደረገውን ጉዞ ለማሳለጥ እንደሚያግዝ በመግለፅ በፈጠራ ሥራም ንቁ የሆኑ ማህበረሰብ በመፍጠር ረገድ ትልቅ ሚና አለው ብለዋል።

በአስጨናቂ ጉዱ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version