አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀዋሳ ከተማ አየተከበረ ባለው ዓመታዊ የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል በተቋቋመ ጊዜያዊ ችሎት አንድ ግለሰብ በሦስት ዓመት እስራት ተቀጣ።
ግለሰቡ ዛሬ ማለዳ ስልክ ነጥቆ ሊያመልጥ ሲል በቁጥጥር ስር መዋሉን የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ኃላፊ ኢንስፔክተር ሽመልስ ብሩ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል።
ከንግስ በዓል ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ የጸጥታና ህገ ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከልና ህግን ለማስከበር ከትላንት ከሰዓት ጀምሮ ጊዜያዊ የምድብ ችሎት ተቋቁሞ እየሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።
በዚህም የተቋቋመው ጊዜያዊ ችሎት ግለሰቡ የፈጸመውን ወንጀል አጣርቶ የሦስት ዓመት እስራት እንደተፈረደበት ማወቅ ተችሏል።
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ ፌደራል ፖሊስ እና የክልል ፖሊስ በጋራ በመሆን ከአንድ ማዕከል በተሰጠ አቅጣጫ የፀጥታ ማስከበር ስራውን እየሰሩ መሆናቸውን ኢንስፔክተር ሽመልስ አስረድተዋል።
ጊዜያዊ ችሎቱም ከሌሎች አካባቢዎች የመጡ እንግዶችን ታሳቢ አድርጎ ፍትህን ለማፋጠን የተቋቋመ ስለመሆኑም ተገልጿል።
በመቅደስ አስፋው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!