Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከተማችንን የምንሰራት ጤናማ ትውልድ እንዲገነባ፣ እንዲረከባት እና እንዲያበለፅጋት ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከተማችንን የምንሰራት ጤናማ ትውልድ እንዲገነባ፣ እንዲረከባት እና እንዲያበለፅጋት ነው አሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

ከተማ አስተዳደሩ በ2017 በጀት ዓመት ከገነባቸው 28 የጤና ፕሮጀክቶች መካከል 22 ያህሉን በዛሬው ዕለት በማስመረቅ ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል።

ፕሮጀክቶቹ የተመረቁት በሁሉም ክፍለ ከተሞች ሲሆን÷ ለአገልግሎት ክፍት የተደረጉ የጤና ጣቢያዎች ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ከመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት ጋር እኩል ደረጃ ያላቸው እንደሆኑ ከንቲባዋ አዳነች ተናግረዋል።

ጤና ጣቢያዎቹ የሚሰጡት አገልግሎት ጥራት ከፍ እንዲል ከ4 ቢልየን በላይ ወጪ የተደረገባቸው በዘመናዊ የህክምና መሳሪያ ግብአት እና ባለሙያዎች ጭምር እንዲደራጁ ተደርገዋልም ነው ያሉት።

እነዚህም ለከተማችን ነዋሪዎች ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጡ፣ ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ እንዲሁም በቅንነት፣ በትጋት እና በታማኝነት የማገልገል ማሳያችን መሆናቸውን አብራርተዋል።

ፕሮጀክቶቹ በጥራትና በፍጥነት ተጠናቅቀው ለሕዝብ አገልግሎት እንዲበቁ ላደረጉት በሙሉ ከንቲባዋ ምስጋና ማቅረባቸውን የከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ለፋና ዲጂታል ገልጿል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version