Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የፋኦ ዋና ዳይሬክተር አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም የእርሻና ምግብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኩ ዶንግዩ በሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት የሥርዓት ምግብ ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የጤና ሚኒስትር ዴዔታ ሰሃርላ አብዱላሂ እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ኢትዮጵያ፣ ከጣሊያን እና ከተባበሩት መንግሥታት ጋር ያዘጋጁት ሁለተኛው የሥርዓተ ምግብ ጉባኤ ከሐምሌ 20 እስከ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

በጉባኤው የሚሳተፉ የሀገራትና ዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች ወደ አዲስ አበባ በመግባት ላይ ይገኛሉ ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

በተመሳሳይ በጉባኤው ለመሳተፍ የኬንያ ቀዳማዊት እመቤት ራቸል ሩቶ አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን፤ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሴቶች እና ማኀበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሩያ አሊ አቀባበል አድርገውላቸዋል ።

Exit mobile version