አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የነሐሴ ወር የቤንዚል፣ የነጭ ናፍጣ፣ የኬሮሲን እና የአውሮፕላን ነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል አለ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፡፡
ሚኒስቴሩ ከዛሬ ምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የነሐሴ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህም መሰረት የቤንዚል፣ የነጭ ናፍጣ፣ የኬሮሲንና የአውሮፕላን ነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ብሏል፡፡
በሌላ በኩል ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 127 ነጥብ 22 ብር እንዲሁም ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 124 ነጥብ 55 ብር ብቻ እንዲሸጥ መወሰኑን የሚኒስቴሩ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ወንድሙ ፍላቴ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡
የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎችም በነዳጅ ውጤቶች ግብይት በአዋጁና በአሠራር መመሪያው መሠረት ውሳኔውን ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡
በኃይለማርያም ተገኝ