Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሆስፒታሉ የተሟላ አገልግሎት እንዲጀምር አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል – አቶ መሀመድ እድሪስ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ እና የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተሟላ አገልግሎት እንዲጀምር አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል አሉ።

አቶ መሀመድ እድሪስ በእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰበትን የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተመልክተዋል።

በሆስፒታሉ ላይ በደረሰው ጉዳት ማዘናቸውን የገለጹት የሰላም ሚኒስትሩ፤ በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት ሳይደርስ አደጋውን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ጥረት ላደረጉ የሕብረተሰብ ክፍሎችና የጸጥታ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

ሆስፒታሉ 97 ዓመታትን ያስቆጠረና ለበርካቶች አገልግሎት የሚሰጥ አንጋፋ መሆኑን አስታውሰው፤ በፍጥነት ወደተሟላ አገልግሎት እንዲመለስ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጋር በመተባበር አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል።

በማቱሳላ ማቴዎስ

Exit mobile version