አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀረሪ ክልል በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ለሚሳተፉ ዳያስፖራዎች ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፡፡
አቶ ኦርዲን በድሪ በአሜሪካ ዳላስ ከተማና አካባቢው ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ባደረጉት ውይይት ስለሀገራዊና ክልላዊ ወቅታዊ ሁኔታ እና እየተካሄደ ስላለው ሁሉን አቀፍ ፈጣን ለውጥ በሚመለከት ለዳያስፖራ ማህበረሰቡ አብራርተዋል፡፡
ዳያስፖራው በሀገሩ ልማት፣ በኢንቨስትመት፣ በዕውቀት ሽግግር፣ በመልካም ገጽታ ግንባታ እና በክልሉ በሚከናወኑ ስራዎች ላይ በንቃት እንዲሳተፍ ጠይቀዋል።
በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ለሚሳተፉ ዳያስፖራዎችም የክልሉ መንግሥት ምቹ ሁኔታዎች መፍጠሩን አንስተዋል።
ዳያስፖራው ለሀገሩ ድልድይ በመሆን በቱሪዝም፣ በንግድ እና ኢንቨስትመንት ዕድገት ላይ ከፍተኛ ሚና መጫወት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በአሜሪካ እና በአካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በክልሉና በሀገር ጉዳዮች ላይ ለመወያየት ላሳዩት ፍላጎትና ተነሳሽነት ማመስገናቸውን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።
የዳያስፖራ አባላቱም በሀገራቸው እና በክልሉ እየተካሄደ ባለው አጠቃላይ እንቅስቃሴ እና እየመጣ ባለው ለውጥ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው÷ በሀገር ጉዳይ በንቃት መሳተፍ እንደሚፈልጉም ተናግረዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!