Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሮሚያ ክልል ሰበታ ክላስተር ሸገር ከተማ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው፡፡

በተከላ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ህብረተሰቡ በንቃት ተሳትፏል።

በሸገር ከተማ ፉሪ ክፍለ ከተማ ገዳ ፉጂ እና ሙዳ ፊሪ በተባሉ አካባቢዎች በተካሄደው የችግኝ ተከላ ከአካባቢው ማህበረሰብ በተጨማሪ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር እና የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከተጠሪ ተቋማቶቻቸው ጋር በመሆን አሻራቸውን አኑረዋል።

በአሸብር ካሳሁን

Exit mobile version