Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በክልሉ የሚቋረጥ ፕሮጀክት እንዳይኖር ህዝቡን ባለቤት ማድረግ ይገባል – አቶ ጥላሁን ከበደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ግብር መክፈል ባህል የማድረግ ትርክት በስፋት መሰራት አለበት አሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ።

የክልሉ ገቢዎች ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀምና በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ በአርባምንጭ ከተማ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

አቶ ጥላሁን ከበደ በዚህ ወቅት ዘርፉ በትብብርና በቅንጅት ሊመራ እንደሚገባ አንስተው÷ የውስጥ አቅምን ከ75 በመቶ በላይ በማሳደግ በድጎማ በጀት ላይ መንጠልጠልን ማቆም እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

በፋይናንስ ምክንያት የሚቋረጥ ፕሮጀክት በክልሉ እንዳይኖር ህዝቡን ባለቤት ማድረግ ይገባልም ነው ያሉት።

በክልሉ ባለፉት ሁለት ዓመታት ገቢ የመሰብሰብ ተግባር እያደገ መምጣቱን አስታውሰው÷ ዘንድሮም ውጤቱን ማስቀጠል እንደሚገባና ህግን የማስከበር ሥራ በልዩ ትኩረት መሰራት እንዳለበት አፅንኦት ስጥተዋል።

የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ በበኩላቸው÷ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 21 ነጥብ 457 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 19 ነጥብ 25 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን ገልጸዋል።

በ2018 በጀት ዓመት 30 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱንም ተናግረዋል።

የቴክኖለጂ ውጤቶች ተግባራዊ መደረጋቸው ለግብር ከፋዮች የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀልጣፋ፣ ከአድሎና ሌብነት የፀዱ ከማድረግ በተጨማሪ ለገቢ አሰባሰቡ ውጤታማነት ትልቅ ድርሻ እንዳለው አመልክተዋል።

ሀገራዊ የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ሙሉ እንዲሆን በክልሉ የተጀመሩ ጠንካራ ሥራዎች ቀጣይነት እንዲኖራቸው ይሰራልም ተብሏል።

በአስጨናቂ ጉዱ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version