Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

እቅዶች ተዘጋጅተው መደበኛ አሠራሮች በመተግበራቸው የተሻለ ውጤት ተመዝግቧል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) እቅዶች ተዘጋጅተው በየጊዜው እየተገመገመ መደበኛ አሠራሮች እየተተገበሩ በመምጣታቸው የተሻለ ውጤት ተመዝግቧል አሉ የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባልና የፌደራል ተቋማት አደረጃጀት ሰብሳቢ አቶ ፍቃዱ ተሰማ።

የብልጽግና ወረዳ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እንዲሁም የ2018 እቅድ ትውውቅ ተካሂዷል።

አቶ ፍቃዱ ተሰማ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ በተካሄደው የአደረጃጀት ማሻሻል ወረዳዎች በተልዕኮ ተቀራራቢ እንዲሆኑ በማስቻል ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ ተቀናጅተው እንዲሰሩ ማድረግ ተችሏል።

እቅዶችን አዘጋጅቶ በየጊዜው እየተገመገመ መደበኛ አሠራሮች እየተተገበሩ በመምጣታቸው የተሻለ ትጋትና ውጤት ተመዝግቧልም ነው ያሉት።

ዓመቱ ምርትና ምርታማነት ማሳደግ የተቻለበት፤ በዲፕሎማሲ ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበት፤ በአረንጓዴ ዐሻራም ከእቅድ በላይ ማሳካት የተቻለበት የማንሰራራት መሆኑን ገልጸዋል።

የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት አባልና የአስተዳደር ክላስተር አስተባባሪ አቶ መለሰ ዓለሙ እያንዳንዱ አባል የጠራ እቅድ በማዘጋጀት መስራት መቻሉና በአመራሩና አባላት ተሳትፎ የታየው መሻሻል ልምድ የሚወሰድበት ነው ብለዋል።

ተቋማት ውጤታማ እንዲሆኑ አመራርና አባላት በግንባር ቀደምነት መስራት ይገባቸዋል ያሉት አቶ መለሰ÷ እያንዳንዱ አባል በተሰማራበት መስክ ውጤታማ በመሆን ቅቡልነትን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል።

በመድረኩ የ2017 እቅድ አፈፃፀም እና 2018 እቅድ እንዲሁም የኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ኮሚሽን ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡ ስኬቶችን ማስቀጠል እና የታዩ ክፍተቶችን በማረም ለላቀ ስኬት መትጋት እንደሚገባም ተገልጿል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version