Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የጣናነሽ ፪ ጉዞ የፅናት፣ ቁርጠኝነትና ቅንጅት አቅም ማሳያ ነው – ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጣናነሽ ፪ ጉዞ የፅናት፣ የቁርጠኝነትና የቅንጅት ታላቅ ምሳሌ ነው አሉ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)።

ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) የጣናነሽ ፪ ከጅቡቲ ዶራሌ ወደብ እስከ ባሕር ዳር የተደረገው ጉዞ እልህ አስጨራሽ ጥረት፣ ፅናትና ቁርጠኝነት የተሞላበት እንደነበር አስታውሰዋል።

በዚህም ጀልባዋ ወደ መዳረሻዋ ባደረገችው የጉዞ ሂደት የተሳተፉ አካላት አስተዋፅዖ የላቀ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ይህንን ታሪካዊ ጉዞ እውን ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ላደረጉ ባለድርሻ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል።

Exit mobile version