Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አዋሽ ባንክ ከ125 ሚሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አዋሽ ባንክ በሐምሌ ወር ከ125 ሚሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ለደንበኞቼ አቅርቤያለሁ አለ፡፡

ባንኩ የደንበኞቹን ፍላጎት ከሟሟላት ጎን ለጎን በሀገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ገልጾ፥ የውጭ ምንዛሪ እጥረትን በዘላቂነት ለመቅረፍና በውጭ ምንዛሪ አደላደል ዙሪያ ግልጽነት እንዲፈጠር ኃላፊነቴን እየተወጣሁ ነው ብሏል፡፡

በዚህም መሰረት ከፈረንጆቹ ከሐምሌ 1 እስከ 31/2025 ድረስ ከደንበኞቹ ከቀረቡ ጥያቄዎች ውስጥ አብዛኛውን ጥያቄዎች በማስተናገድ በድምሩ ከ125 ሚሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ለደንበኞቹ ማቅረቡን ገልጿል፡፡

ከዚህም ውስጥ ከ70 ሚሊየን ዶላር በላይ ለነዳጅ ግዢ ያቀረበው ሲሆን፥ ቀሪውን ከ55 ሚሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምዛሪ ወደ ሃገራችን የሚገቡ ስልታዊ ሸቀጦች መስጠቱን ነው ባንኩ ያስታወቀው፡፡

የደንበኞቹን የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችል አቅርቦት እንዳለው ጠቅሶ፥ በተለይም ለትምህርት፣ ለህክምናና መሰል ክፍያዎች ቅድሚያ በመስጠት የውጭ ምንዛሪ ድልድል ማድረጉን እንደሚቀጥል ገልጿል፡፡

Exit mobile version