አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ክልል ቱሪዝም ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር የነበሩት ዳውድ ሙሜ ሥርዓተ ቀብር በዛሬው ዕለት በኮልፌ ሙስሊም መካነ መቃብር ተፈጽሟል።
አቶ ዳውድ ሙሜ በትናንትናው ዕለት ከአዲስ አዳማ የፍጥነት መንገድ ላይ ባጋጠማቸው የመኪና አደጋ ሕይወታቸው አልፏል።
ኮሚሽነር ዳውድ ሙሜ ባለትዳር እና የ4 ልጆች አባት ነበሩ።
ሥርዓተ ቀብራቸው ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ ቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ተፈጽሟል።