Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሙስናን ለመከላከል የትውልድ ሥነ ምግባር ግንባታ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፌዴራል የሥነ ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ሙስናን ለመከላከል የትውልድ ሥነ ምግባር ግንባታ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት አለ።

14ኛ ሀገር አቀፍ የጸረ ሙስና ኮሚሽኖች ትስስር ጉባኤ የሁሉም ክልሎች የዘርፉ ኮሚሽነሮች በተገኙበት በጅማ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ እንዳሉት፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተጀመረው የጸረ ሙስና እንቅሰቃሴ ለውጥ መታየት ጀምሯል።

በሙስና የባከነ ሀብት እየተመለሰና ወንጀለኞች እየተቀጡ ነው ብለዋል።

ሙስናን በመከላከል ረገድ የሚታየውን ክፍተት ለመሙላትና የትውልድ ሥነ ምግባር ግንባታ ስራውን አጠናክሮ ለማስቀጠል ከባለድርሻ አካላት ጋር በትትብብር እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

ዜጎች በትክክለኛ ሥነ ምግባር ለእውነት የሚሰሩና የሚኖሩ፣ የሀገራቸውንና የቤተሰባቸውን ሀብት የማይሰርቁ፣ በሰሩትና በለፉት ልክ ለመክበር የሚተጉ እንዲሆኑ በሥነ ምግባር ግንባታ ላይ መስራት ያስፈልጋል ነው ያሉት።

በመድረኩ የ2017 በጀት ዓመት ሥራ አፈፃፀም እንደሚገመገም እና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት ይደረጋል።

በተስፋሁን ከበደ

Exit mobile version