Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የቀድሞ የፋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ ገሰሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቀድሞ የሬድዮ ፋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ ገሰሰ በ66 ዓመታቸው በትናንትናው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

አቶ ሙሉጌታ ከሬድዮ ፋና መስራች አመራሮች ውስጥ አንዱ የነበሩ ሲሆን፥ ከዚህም በተጨማሪ በኢትዮጵያ ሬድዮና በሜጋ አሳታሚ ድርጅት በኃላፊነት አገልግለዋል፡፡

አቶ ሙሉጌታ የአንድ ሴት እና የሁለት ወንድ ልጆች አባት የነበሩ ሲሆን፥ በቢዝነስ አድሚኒስተሬሽን የሁለተኛ ዲግሪያውን በእንግሊዝ ሀገር ተከታትለዋል፡፡

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በአቶ ሙሉጌታ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለጸ፥ ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል፡፡

Exit mobile version