Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሀረሪ ክልል አርሶ አደሩን ከተረጂነት ለማላቀቅ በተሰሩ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት ተገኝቷል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀረሪ ክልል አርሶ አደሩን ከተረጂነት ለማላቀቅ የተሰሩ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት አስገኝተዋል አሉ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ሮዛ ኡመር፡፡

በክልሉ ለ200 አባወራ አርሶ አደሮች 84 ሚሊዮን ብር የሚገመት የውሃ መሳቢያ ሞተር፣ የአፈር ማዳበሪያ፣ የምርጥ ዘርና ሌሎች የግብርና ግብዓት ድጋፎች ተደርገዋል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሯ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ በክልሉ የሴፍቲኔት ተረጂ አርሶ አደሮችን በመለየት ተደራጅተው ማምረት እንዲችሉ የስልጠናና የግብዓት ድጋፍ በማድረግ ከተረጂነት እንዲወጡ ለማስቻል እየተሰራ ነው።

በዚህም አርሶ አደሩን ከተረጂነት ለማላቀቅ የተሰሩ ስራዎች ተጨማጭ ውጤት አስገኝቷል ነው ያሉት።

የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ጌቱ ወዬሳ በበኩላቸው፥ በክልሉ አርሶ አደሩን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለማሸጋገር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በተስፋዬ ሀይሉ

Exit mobile version