አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኒውካስል ዩናይትድ እንግሊዛዊውን ግብ ጠባቂ አሮን ራምስዴልን ከሳውዝሃምፕተን በውሰት ውል አስፈርሟል።
ኒውካስል ዩናይትድ የቀድሞ የመድፈኞች ግብ ጠባቂ አሮን ራምስዴልን የመግዛት አማራጭ ባለው የውሰት ውል ነው ያስፈረመው።
የ27 ዓመቱ ግብ ጠባቂ በኒውካስል ዩናይትድ ቤት ለአንድ ዓመት የሚያቆየውን ውል ተፈራርሟል።
ራምስዴል በኒውካስል ዩናይትድ ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ ለመሆን ከኒክ ፖፕ ጋር ይፎካከራል።
ግብ ጠባቂው በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በሳውዝሃምፕተን ማሳለፉ ይታወሳል።
በዮናስ ጌትነት