Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሀገርን በማረጋጋት ለቀጣዩ ትውልድ በማስተላለፍ ሂደት ውስጥ የሐይማኖት ተቋማት ሚና ከፍተኛ ነው- ቀሲስ ታጋይ ታደለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀገርን በማረጋጋት ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ በሚደረገው ጥረት የሐይማኖት ተቋማት ሚና ከፍተኛ ነው አሉ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ዋና ጸሃፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ፡፡

4ኛው ሃገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ ”ሐይማኖት ለሰላም፣ ለአንድነተትና ለመከባበር” በሚል መሪ ሃሳብ በሐረር ከተማ እየተካሄደ ነው።

ቀሲስ ታጋይ ታደለ በኮንፈረንሱ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ÷ አባቶች ጠብቀው ያቆዩት ሐይማኖታዊ እሴት እንዳይሸረሸር የሐይማኖት ተቋማት የበኩላቸውን መወጣት  እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ከመገፋፋትና ከመበሻሸቅ በመውጣት ተከባብሮ መኖር ያስልጋል ያሉት ዋና ጸሐፊው÷ከሃገር አቀፉ የሰላም ኮንፈረንስም ለኢትዮጵያ መፍትሄ የሚሆን የጋራ ሀሳብ  ይጠበቃል ብለዋል።

የሀረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ኡመር በበኩላቸው÷ሰላም ለሁሉም ነገር መሠረት መሆኑን በመጥቀስ÷ሁሉም የሐይማኖት ተቋማት ብሔራዊ አንድነትን ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡

ስላም የሚጀምረው በእያንዳንዱ ዜጋ ውስጥ መሆኑንም ነው ያመላከቱት፡፡

በሰላም ኮንፈረንሱ የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት የሐይማኖት አባቶች ከፍተኛ  የመንግስት የሥራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የሁሉም ክልል የሐይማኖት ተቋማት የሐይማኖት መሪዎች የሃገር ሽማግሌዎች እንዲሁም አጋር አካላትና የሐረር ከተማ ነዋሪዎች እየተሳተፉ ነው።

በየሻምበል ምህረት

Exit mobile version