Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

 የኢትዮጵያ እና የደቡብ አፍሪካ ካራቴ ፌደሬሽኖች በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ እና የደቡብ አፍሪካ የካራቴ ፌዴሬሽኖች በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል።

የኢትዮጵያ ካራቴ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሙሉነህ ጎሳዬ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ስምምነቱ ኢትዮጵያውያን የካራቴ ስፖርት ባለሙያዎች የሙያ እድገት ስልጠና እንዲያገኙ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ታምኖበታል፡፡

ኢትዮጵያ በደቡብ አፍሪካ በሚደረጉ የተለያዩ የካራቴ ውድድሮች ላይ እንድትሳተፍና ትልልቅ ውድድሮችን በብቃት እንድታዘጋጅ የሚያግዝ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የዓለም የካራቴ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንትና የደቡብ አፍሪካ የካራቴ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሶኒ ፕሌይ በበኩላቸው፥ በቀጣይ ኢትዮጵያ በስፖርቱ ላይ በትኩረት እንድትሰራ እገዛ እናደርጋለን ብለዋል።

በዳንኤል እንዳለ

Exit mobile version