አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፖርቹጋላዊው የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ሩበን ዲያዝ በማንቼስተር ሲቲ ለረጅም ዓመታት ለመቆየት ውሉን ለማራዘም ተስማምቷል፡፡
ሩበን ዲያዝ በማንቼስተር ሲቲ እስከ ፈረንጆቹ 2027 የሚያቆይ ኮንትራት ቢኖረውም ለተጨማሪ ዓመታት ለመቆየት መስማማቱን ዘ አትሌቲክስ ዘግቧል፡፡
የ28 ዓመቱ ሩበን ዲያዝ ከማንቼስተር ሲቲ ጋር የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግን ጨምሮ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ፣ ኤፍ ኤ ካፕ፣ ካራባኦ ካፕ እና የአውሮፓ ሱፐር ካፕ ዋንጫዎችን አሳክቷል፡፡
ሩበን ዲያዝ ከፖርቹጋሉ ክለብ ቤኔፊካ ማንቼስተር ሲቲን ከተቀላቀለ በኋላ ስኬታማ ዓመታትን በውሃ ሰማያዊዎቹ ቤት እያሳለፈ ይገኛል፡፡
በወንድማገኝ ጸጋዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!