አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የኮንስትራክሽን ዘርፉን ስራ ለማዘመን እና ለማፋጠን የሚያስችል “ፉርቱ” የተሰኘ መተግበሪያን አገልግሎት አስጀምሯል።
መተግበሪያው ደንበኞች የሚፈልጉትን አገልግሎት ከሰው ንክኪ ነፃ በሆነ መንገድ በያሉበት እንዲያገኙ የሚያስችል እንደሆነ ተመላክቷል።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ናትናኤል ጌታሁን (ኢ/ር) አዲሱ መተግበሪያ ተግባራዊ የተደረገው ማሕበረሰቡ ከመደበኛ የስራ ቦታቸው ሆነው አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ ለማድረግ ነው ብለዋል።
መተግበሪያው ከዛሬ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርና ተገልጋዮችም በቴክኖሎጂው በመታገዝ ከሚሰጡ አገልግሎቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ባለስልጣኑ ከዚህ በፊት ለአገልግሎት አሰጣጥ ምቹ ያልሆነውን የስራ ቦታ በዘመናዊ መንገድ በማደስ ቢሮውን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
በዳሳለኝ አበራ