አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቀድሞ እግር ኳስ ኮከቡ ጆርጅ ዊሃ ልጅ ቲሞቲ ዊሃ የፈረንሳዩን ክለብ ኦሎምፒክ ደ ማርሴን በይፋ ተቀላቅሏል፡፡
የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋች ቲሞቲ ዊሃ ከጣሊያኑ ክለብ ጁቬንቱስ ወደ ኦሎምፒክ ደ ማርሴ አምርቷል፡፡
የ25 ዓመቱ ተጫዋች በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ለጁቬንቱስ ባደረጋቸው 30 የጣሊያን ሴሪ አ ጨዋታዎች አምስት ግቦችን አስቆጥሮ ሁለት ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ አቀብሏል፡፡
ቲሞቲ ዊሃ በ2023/24 የውድድር ዓመት ከፈረንሳዩ ክለብ ሊል ጁቬቱስን መቀላቀቀሉ ይታወሳል፡፡
ከእግር ኳስ ህይወቱ በኋላ ወደ ፖለቲካው ዓለም በመግባት ሀገሩን ላይቤሪያ በፕሬዚዳንትነት ያገለገለገው አባቱ ጆርጅ ዊሃ የባሎንዶር ሽልማትን ያሸነፈ ብቸኛ አፍሪካዊ ተጫዋች መሆኑ ይታወቃል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!