Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ በደረሰ የመኪና አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ

‎አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ በደረሰ የመኪና አደጋ የአምስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ሦስት ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሷል።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ ኮማንደር በለጠ ተ/ስላሴ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ የመኪና አደጋው ከአዲስ አበባ ወደ ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ሲጓዝ የነበረ ተሳቢ መኪና ከለሚ ከተማ ስድስት ሰዎችን አሳፍሮ ወደ ወቀሎ አንጾኪያ ቀበሌ እየተጓዘ ያለውን ባለ ሦስት አግር ተሽከሪካሪ (ባጃጅ) ጋር ቢረሙ ቀበሌ ላይ ተጋጭቶ ነው።

በዚህም ባለ ሦስት አግር ተሽከሪካሪውን ከመንገድ ውጪ በማስፈንጠር የተከሰተ አደጋ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በአደጋው የባጃጁን አሽከርካሪ ጨምሮ የአምስት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በሁለት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳትና በአንድ ሰው ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱን ጠቁመዋል፡፡

በተሳቢ የመኪና አሽከርካሪ ላይ ቀላል ጉዳት እንደደረሰም አስረድተዋል።

ለአደጋው መንስዔ የሆነው ጭጋጋማ የአየር ንብረት እንደሆነ በመግለጽ ቆሞ የነበረ ተሳቢ መኪና ከኋላ በመጣ ተሳቢ መኪና በመገጨቱ ከኋላ በገጨው ተሳቢ ላይ የንብረት ጉዳት መድረሱንም ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ የትራፊክ አደጋውን ለመከላከል የከተማ ፓርኪንግና ሌሎች ለትራፊክ ፍሰት እንቅፋት የሚሆኑ ተግዳሮቶችን በዘላቂነት ለመቅረፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር ይሰራል ያሉት ኮማንደር በለጠ÷ አሽከርካሪዎች በሚያሽከረክሩበት ወቅት ለሰው ህይወት ቅድሚያ በመስጠት ከመሰል የትራፊክ አደጋ ራሱንና ማሕበረሰቡን እንዲጠብቅና የወቅቱን አየር ሁኔታ ታሳቢ አድርገው በጥንቃቄ እንዲያሽከረክሩም አሳስበዋል።

በአድማሱ አራጋው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version